በ3rd Ave S እና S Main St የአውቶቡስ ማቆሚያ

繁体字 • 日本語 • 한국어 • af-Soomaali • Español • Tagalog • Tiếng việt • English

ነሐሴ 2 ቀን 2022

አሁን ምን እየሆነ ነው ያለው?

የበለጠ ደህንነቱ የተጠበቀ በS Washington St እና S Main St መካከል ባለው የ3ኛው ጎዳና ደቡብ ላይ ባለው የአውቶቡስ ማቆሚያ ላይ፣ አውቶቡስ ለሚጠብቁ ሰዎች፣ የበለጠ ተደራሽ እና የበለጠ ምቹነት ያለው ተሞክሮ ለመፍጠር ማሻሻያዎችን እየነደፍን ነው። ፕሮጀክቱ የተሻለ የሚሰራ የአውቶቡስ ማቆሚያ በመፍጠር እና መንገዱን በመጠገን እና በማስተካከል የአውቶቡስ ጉዞ ጊዜን እና አስተማማኝነትን ለማሻሻል ይረዳል።

የጊዜ ሰሌዳው ሊቀየር ይችላል፣ ነገር ግን የፕሮጀክት ንድፉን በ2023 አጋማሽ አጠናቅቀን በ2024 አጋማሽ ግንባታውን እንደምናጠናቅቅ እንጠብቃለን

የፕሮጀክት አጠቃላይ እይታ

ይህንን ፕሮጀክት ከኪንግ ካውንቲ ሜትሮ ጋር በመተባበር ንድፉን እና ትግበራውን እየሰራን ነው። ይህ በ2015 የተጀመረው ፕሮጀክት፣ መጀመሪያ እንደ የሶስተኛ ጐዳና ትራንዚት ኮሪደር ማሻሻያ ፕሮጀክት አካል ሆኖ ታውቆ ነው። የሶስተኛ ጐዳና ትራንዚት ኮሪደር Belltown፣ የማዕከላዊ ንግድ ወረዳን እና Pioneer Squareን በማገናኘት፣ ከDenny Way እስከ S Jackson St ድረስ ይዘልቃል። 

በእያንዳንዱ ቀን የሶስተኛ ጐዳና ትራንዚት ኮሪደሩን 65,000 በእግር የሚራመዱ እና የሚያንከባልሉ ሰዎች ይጠቀማሉ፣ እና በአውቶቡሱ ለሚሳፈሩ ሰዎች በከተማው እና በክልል ውስጥ የሕዝብ መተላለፊያ ግንኙነቶችን ያቀርባል። ወረርሽኙ ከመከሰቱ በፊት፣ በየቀኑ ከ100,000 በላይ ሰዎችን በማንቀሳቀስ ከ2,500 በላይ አውቶቡሶች በሶስተኛው ጎዳና ይጠቀሙ ነበር። ወደ 20 የሚጠጉ የተለያዩ የአውቶቡስ መስመሮች የሚያገለግሉ 850 አውቶቡሶች በየቀኑ በ 3rd Ave S እና S Main St አውቶቡስ ማቆሚያውን ይጠቀማሉ። በ2020 ፀደይ፣ ይህ የአውቶቡስ ማቆሚያ የኪንግ ካውንቲ ሜትሮ በእያንዳንዱ የሳምንት ቀናት ከ3,000 በላይ ተጠቃሚዎች ያለው ስድስተኛው በጣም የተጨናነቀ ማቆሚያ ነበር። 

አሁን በ 3rd Ave S እና S Main St ላይ ያለው የአውቶብስ ፌርማታ በአሁኑ ጊዜ ለእንደዚህ አይነት ስራ የሚበዛበት የአውቶቡስ ማቆሚያ ተደራሽነት እና የንድፍ ገፅታዎች ይጎድለዋል። ካለው የአጐራባች የመኪና ማቆሚያ ቦታ መለያ የሌላቸው ጠባብ የእግረኛ መንገዶች (9-11 ጫማ) አሉ። በተወሰነ መብራት፣ መቀመጫ የሌለው እና የኤሌክትሪክ ሃይል የሌለው አንድ የአውቶቡስ መጠለያ ብቻ አለ። በአውቶቡስ ማቆሚያ ላይ የሚደረጉ ማሻሻያዎች የእግረኛ መንገዶችን ማስፋት፣ የእግረኛ መሻገሪያ መንገዶችን እንደገና መቀባት፣ የእግረኛ መብራት መጨመርን፣ አዳዲስ ዛፎችን መትከል እና ሌሎች የአውቶቡስ ማቆሚያ አገልግሎቶችን ያካትታሉ: 

  • የአውቶቡስ መጠለያዎች
  • መቀመጫ 
  • ትክክለኛ ተጨባጭ የአውቶቡስ ጊዜ መድረሻ መረጃ 
  • የORCA ካርድ አንባቢ

አውቶቡሶች በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጓዙ እንዲረዳ መንገዱን በአዲስ የቅጥራን/ ሲሚንቶ ንጣፍ ጠግነን እና መንገዱ ወደ ደቡብ አቅጣጫ ብቻ እንዲሆን እንደገና እናስተካክለዋለን። አሁን ያለው ከመንገዱ በምስራቅ በኩል የሚገኘው የመንገድ ላይ የመኪና ማቆሚያ እንዳለ ይቆያል ነገር ግን ለአዲሱ ለደቡብ-አቅጣጫ ብቻ የመንገድ ንድፍ አቅጣጫው ይቀለበሳል። 

በ 3rd Ave S እና S Main St ያለው የዝናብ ፍሳሽ ማሻሻያ ስራዎችም ከሲያትል የህዝብ መገልገያዎች የአንድ ቦታ ፍሳሽ ጥገና ፕሮግራም ደግሞ በዚህ ፕሮጀክት እንደገና በመጠናቀቅ ላይ ናቸው።  

የፕሮጀክት አካባቢ

በS Washington St እና በS Main St መካከል በ3ኛው ጎዳና ደቡብ በስተምዕራብ በኩል የሚገኘውን የአውቶቡስ ማቆሚያ እያሻሻልን ነው።

በS Washington St እና በS Main St መካከል በ3ኛው ጎዳና ደቡብ በስተምዕራብ በኩል የታቀደው የአውቶቡስ ማቆሚያ የሚገኝበትን ቦታ የሚያሳይ ምስላዊ ካርታ። ለPDF እትም ጠቅ ያድርጉ።

ነባር/ አሁን ያለው የመንገድ ንድፍ:  

በታቀደው የአውቶቡስ ማቆሚያ ዙሪያ ያሉትን የእግረኛ መንገዶችን፣ የብስክሌት ብቻ መስመሮችን፣ የመታጠፊያ መስመሮችን እና የሲያትል ዩኒየን የወንጌል ተልእኮ መገልገያዎችን ጨምሮ፣ ነባር የሰፋፊ መንገዶችን እና የከተማ ክፍልፋይ ማዕዘናት ገፅታዎችን የሚያሳይ ምስላዊ ካርታ። ለትልቅ የPDF እትም ጠቅ ያድርጉ።

 አሁን ባለው ፌርማታ/ ማቆሚያ ጋ በቅጥራን/ ሲሚንቶ የምንጠግነው የተበላሸ የመንገድ ምስል።ስዕሉ ከላይ የሚታየው: በቅጥራን/ ሲሚንቶ የምንጠግነው የተበላሸ ጎዳና።   

አሁን ባለው የአውቶቡስ ፌርማታ መጠለያ ላይ ወደታች ሲታይ ከአንድ ኩርባው ላይ ካለ አውቶብስ ጋር 3ኛ የተነሳው ፎቶ።

ስዕሉ ከላይ የሚታየው: በነባሩ የአውቶቡስ ማቆሚያ ላይ የሚጠብቁ ሰዎች

የወደፊቱ የመንገድ ንድፍ:  

ሰፋ ያለ የእግረኛ መንገድ፣ አዳዲስ ዛፎች፣ የኮንክሪት አውቶቡስ ንጣፍ እና ከመብራት ጋር አዲስ የመጠለያ በ3ኛ እና በMain ላይ ያለውን የአውቶቡስ ማቆሚያ ለማሻሻል የታቀዱት ባህሪያት ያሉበትን ቦታዎች የሚያሳይ ምስላዊ ካርታ።

የፕሮጀክት መርሃ ግብር

ከዚህ ከታች ያለው መርሐግብሩ የታቀዱትን አዳዲስ ታሪካዊ ክንውኖችን ያሳያል እና ሊለወጥ ይችላል:

    • ሀምሌ 2022: 30% ንድፍ
    • ሚያዚያ 2023: 60% ንድፍ 
    • ሰኔ 2023: 90% ንድፍ
    • ነሐሴ 2023: የመጨረሻ ንድፍ 
    • በ2024 መጀመሪያ: ግንባታው ይጀመራል
    • 2024 በጋ: ግንባታ ይጠናቀቃል 

የገንዘብ ድጋፍ

ይህ ፕሮጀክት በአብዛኛው የሚሸፈነው ከፌዴራል የሕዝብ ማመላለሻ አስተዳደር በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ነው።  በፌዴራል የሕዝብ ማመላለሻ አስተዳደር (FTA) የሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ በS Washington እና S Main St መካከል በ 3rd Ave S ላይ ማሻሻያዎችን ብቻ ይሸፍናል። ተጨማሪ የገንዘብ ምንጮች አንቀሳቅስ ሲያትል ቀረጥ (Move Seattle Levy)፣ ኪንግ ካውንቲ ሜትሮ እና የሲያትል የህዝብ የፍጆታ መገልገያዎችን ያካትታሉ።

የፕሮጀክት የመረጃ ግብአቶች

የፕሮጀክት የመረጃ ግብአቶች እየተደራጁ ሲመጡ ይጋራሉ (መረጃቸው)። 

ተዛማጅ ፕሮጀክቶች 

Transportation

Greg Spotts, Director
Address: 700 5th Ave, Suite 3800, Seattle, WA, 98104
Mailing Address: PO Box 34996, Seattle, WA, 98124-4996
Phone: (206) 684-7623
684-Road@seattle.gov

Newsletter Updates

Subscribe

Sign up for the latest updates from Transportation

The Seattle Department of Transportation (SDOT) is on a mission to deliver a transportation system that provides safe and affordable access to places and opportunities for everyone as we work to achieve our vision of Seattle as a thriving, equitable community powered by dependable transportation.