Seattle Sidewalk Accessibility Guide

ሰዎች የሲያትል የእግረኛ መንገዶችን በእግር ለመራመድ፣ ለመሮጥ፣ ለማንከባለል እና ለመጫወት ይጠቀማሉ። በአንዳንድ ሁኔታዎች፣ በእንቅፋቶች፣ በመልካም ሁኔታ ላይ ባለመሆናቸው እና በጠፉ የእግረኛ መንገዶች ምክንያት ሰዎች በቀላሉ በእግረኛ መንገዶች መዳረስ አይችሉም። በተለይም በሰሜን እና በደቡብ ሲያትል እና በኢንዱስትሪ ወረዳዎቻችን፣ ወደ 24% የሚጠጉ መንገዶች የእግረኛ መንገድ የላቸውም። የሲያትል የእግረኞች ዋና ዕቅድ (PMP) እና የPMP የትግበራ እቅድ በአዲስ የጐን እግረኛ መንገዶች እና የመራመጃ መንገዶች ላይ የኛን መዋዕለ ንዋዮቻችንን ይመራሉ። PMP ሲያትልን በብሔሩ ውስጥ በጣም መራመድ የሚቻልበት እና ተደራሽ ከተማ ተደርጎ እንደሚታይ ነው። ሰዎች በበለጠ ቁጥር በደህና እና በደስታ እንዲራመዱ እንፈልጋለን። በእግር መሄድ በጣም ተደራሽ የሆነው የመጓጓዣ መንገድ እና የመዝናኛ አይነት እንደመሆኑ ጥራት ያለው በዋናው ላይ አንድ የእግረኞች ፍትሃዊ እኩልነት ያለው አውታረ መረብ እና ተደራሽ የሆነ የማመላለሻ ስርዓት መሰረት ነው።

ሲያትል ሰዎች በደህና እንዲመላለሱ እና በከተማው እንዲዘዋወሩ የሚረዳ ወደ 2,300 ማይል የሚጠጋ የዳር እግረኛ መንገድ አለው። ጥገናዎች ብዙውን ጊዜ የንብረቱ ባለቤት ኃላፊነት ቢሆንም (የእግረኛ መንገድ ምርምሮችን ይመልከቱ)፣ እንደ የአስፋልት ቀለበቶች እና ስላች የተቆረጡ ያሉ ደህንነቱ የተጠበቀ መተላለፊያን ለመጠበቅ ጊዜያዊ እርምጃዎችን ልንጠቀም እንችላለን። ለበለጠ መረጃ የጐን እግረኛ መንገድ ጥገና ፕሮግራም ድህረ ገጽን እና የጥገና ፕሮግራም የታሪክ ካርታን ይጎብኙ። አገልግሎት ለመጠየቅ፣ ከታች ባሉት ማናቸውም ዘዴዎች ያግኙን።

ይህን መመሪያ የጐን እግረኛ መንገዶችን በተሻለ ሁኔታ ለመንከባከብ ምን ማድረግ እንደምንችል የንብረት ባለቤቶችን፣ ተከራዮችን፣ ተቋራጮችን እና ተጓዡን ሕዝብ ለማስተማር እንዲረዳ የፈጠርነው ነው። ለመጀመር፣ ከታች ካሉት የተጠቃሚ ሚናዎች ውስጥ አንዱን ጠቅ ያድርጉ። በዚህ መመሪያ ላይ ጥያቄዎች ካሉዎት በ SDOTAssets@seattle.gov ያግኙን።

የቤት ባለቤት ኃላፊነቶች

እፅዋት፣ ዛፎች፣ ታጣፊ ሰሌዳዎች፣ ምልክቶች እና የመገልገያ ምሰሶዎች ሰዎች በእግረኛ መንገዳችን ላይ እንዳይዞሩ አስቸጋሪ ያደርጉታል። እነዚህን ነገሮች በመተላለፊያው ላይ ያሉ ቋሚ እና ጊዜያዊ እገዳዎች ተደራሽነትን "የሚያስተጓጉሉ/ እንቅፋቶች" ብለን እንጠራቸዋለን። የእግረኛ መንገድን ስፋቱን ከ36 ኢንች ባነሰ የሚወስን እንደ ብስክሌቶች እና ስኩተሮች ያሉ የሚገድቡ ማንኛቸውም ነገር እንደ አንድ እንቅፋት/ አስተጓጓይ ሊቆጠር ይችላል።

የሲያትል ማዘጋጃ ቤት ህግ (SMC) አርእስት 15 ለሁሉም የእግረኛ መንገድ ተጠቃሚዎች የህዝብ ጉዞን ለማበረታታት የንብረት ባለቤቶች ከንብረታቸው አጠገብ ያለውን የጐን እግረኛ መንገዱን ለድህንነት እና በጥሩ ሁኔታ እንዲጠብቁ ያስገድዳል። ለተጨማሪ ዝርዝሮች የኛን የንብረት ባለቤቶች ሃላፊነቶች ጣቢያ ይጎብኙ እና የጐን እግረኛ መንገዶችን የተጋለጠ ማድረግ እና ለመጠገን መመሪያችንን ይመልከቱ።

የተከራይ ኃላፊነቶች

ሰዎች ለመራመድ፣ ለመሮጥ፣ ለማንከባለል፣ ወዘተ እንዳይችሉ ተክሎች፣ ዛፎች፣ ታጣፊ ሰሌዳዎች፣ ምልክቶች እና የመገልገያ ምሰሶዎች አስቸጋሪ ያደርጉታል። እንደነዚህ አይነት በተጠቃሚዎች የጐን እግረኛ መንገድ ላይ የጣልቃ ገብነቶች ገጠመኞችን እንደ ቋሚ እና ጊዜያዊ "እንቅፋቶች" እንጠቅሳቸዋለን ምክንያቱም በመተላለፊያው ላይ ያለውን ተደራሽነት ስለሚገድቡ። የእግረኛ መተላለፊያውን ስፋት ከ36 ኢንች በታች እንዲሆን የሚገድብ ማንኛቸውም ነገር እንደ እንቅፋት/ አስተጓጓይ ሊቆጠር ይችላል። የሲያትል ማዘጋጃ ቤት ህግ (SMC) አርእስት 15 ለሁሉም የእግረኛ መንገድ ተጠቃሚዎች የህዝብ ጉዞን ለማበረታታት የንብረት ባለቤቶች ከንብረታቸው አጠገብ ያለውን የጐን እግረኛ መንገዱን ለድህንነት እና በጥሩ ሁኔታ እንዲጠብቁ ያስገድዳል። የእግረኛ መንገዶችን ነፃ ስለማድረግ መመሪያችንን ከዚህ በታች ይመልከቱ።

የንግድ ሥራ ኃላፊነቶች

ሰዎች ለመራመድ፣ ለመሮጥ፣ ለማንከባለል፣ ወዘተ እንዳይችሉ ተክሎች፣ ዛፎች፣ ታጣፊ ሰሌዳዎች፣ ምልክቶች እና የመገልገያ ምሰሶዎች አስቸጋሪ ያደርጉታል። እንደነዚህ አይነት በተጠቃሚዎች የጐን እግረኛ መንገድ ላይ የጣልቃ ገብነቶች ገጠመኞችን እንደ ቋሚ እና ጊዜያዊ "እንቅፋቶች" እንጠቅሳቸዋለን ምክንያቱም በመተላለፊያው ላይ ያለውን ተደራሽነት ስለሚገድቡ። እንደ እውነቱ፣ የእግረኛ መተላለፊያውን ስፋት ከ36 ኢንች በታች እንዲሆን የሚገድብ ማንኛቸውም ነገር፣ እንደ ብስክሌቶች እና ስኩተሮች ያሉ ሁሉ፣ እንደ እንቅፋት ሊቆጠር ይችላል። የሲያትል ማዘጋጃ ቤት ህግ (SMC) አርእስት 15 ለሁሉም የእግረኛ መንገድ ተጠቃሚዎች የህዝብ ጉዞን ለማበረታታት የንብረት ባለቤቶች ከንብረታቸው አጠገብ ያለውን የጐን እግረኛ መንገዱን ለድህንነት እና በጥሩ ሁኔታ እንዲጠብቁ ያስገድዳል። የጐን እግረኛ መንገዶችን የተጋለጠ ለማድረግ እና ለመጠገን ለበለጠ ዝርዝሮች መረጃ እና ከዚህ በታች ያለንን መመሪያ ለማግኘት የንብረት ባለቤቶቸን ሃላፊነት ጣቢያችንን ይጎብኙ።

እፅዋትን መጠበቅ እና ፍርስራሾችን ማስወገድ

የንብረት ባለቤቶች እፅዋትን ቢያንስ ከ8 ጫማ የጐን እግረኛ መንገድ በላይ፣ ከ14 ጫማ ከኩርባ በላይ እና ከጐን እግረኛ መንገዱ ጫፍ ቢያንስ 1 ጫማ ወደኋላ መመለስ አለባቸው። ለበለጠ መረጃ የሲያትል የግንባታ እና የቁጥጥሮች መምሪያ ጥቆማ 611 ላይ የአረምና ዕፅዋት አፈጻጸምን ማስከበርን ይመልከቱ።

ለእግረኛ መንገድ አስፈላጊ የሆነውን እጽዋቱ ነፃ የተደረጉበት ቦታን የሚያሳይ የመሬት አቀማመጥ፣ ዛፎች፣ የእግረኛ መንገዶች፣ መንገድ፣ እና ትራፊክ አቋራጭ የግራፊክ ክፍል። በጐን የእግረኛ መንገዱ ላይ አንድ ከዘራ የያዘ ሰው እና አንድ በተሽከርካሪ ወንበር ውስጥ ያለ ሰው አሉ። በመንገዱ ላይ አንድ የጭነት መኪና አለ።

የጐን እግረኛ መንገድ የእፅዋት ነፃ መደረግ ግራፊክ።

ተክሎች፣ ዛፎች፣ ቅጠሎች፣ ልቅ ጠጠር እና ፍርስራሾች በእግረኞች ላይ ችግር ሊፈጥሩ ይችላሉ። እያንዳንዱ ሰው እና ጎረቤቶቻቸውም የጐን እግረኛ መንገዶቻቸውን ከላይ ወለሉ ሁኔታዎች እና እንቅፋቶች/ አስተጓጓዮች ማጽዳት አለባቸው።

የእግረኛ መንገድ በከፊል በዘሌ ቁጥቋጦዎች ተዘግቷል። የመሬት አቀማመጥ አካባቢ እና በቀኝ በኩል መንገድ። የእግረኛ መንገድ ሙሉ በሙሉ በቁጥቋጦዎች የተደናቀፈ እና በከፊልነት በፍርስራሾች የተሸፈነ። የመሬት አቀማመጥ አካባቢ እና በቀኝ በኩል መንገድ።

እየተባባሰበት፣ አምባር/ ቡናማ ብጫ ቀለም ባላቸው ቅጠሎች የተሸፈነ የእግረኛ መንገድ  በበረዶ እና በቅጠል ርጋፊዎች የተሸፈነ የእግረኛ መንገድ አምባር/ ቡናማ ብጫ ቀለም ባላቸው ቅጠሎች የተሸፈነ የእግረኛ መንገድ  

ከላይ ያሉት ምስሎች ሰዎች የእግረኛ መንገድዎን ለመጠቀም ሲሞክሩ የሚያጋጥሟቸው አንዳንድ ተግዳሮቶችን ያሳያሉ።

የእግረኛ መንገድ እፅዋት እና ርጋፊ ቆሻሻ የማጽዳት ፕሮግራሞች

Adopt-a-Street! ወይም የጸደይ ማጽዳት ውስጥ በመሳተፍ የሲያትል መንገዶችን እና የእግረኛ መንገዶችን ከቆሻሻ ነጻ ያድርጉ። Adopt-a-Street የሲያትል ሥረ-መሰረታዊ ቆሻሻን የማስወገድ ፕሮግራም ነው። በመቶዎች የሚቆጠሩ ማይሎችን የሲያትል ከተማ መንገዶችን እና የእግረኛ መንገዶችን የሚያጸዱ በሺዎች የሚቆጠሩ በጎ ፈቃደኞችን ይቀላቀሉ። ስለ ዛፍ ማስተካከል/ መግረዝ እና ፍቃዶች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የዛፍ እንክብካቤ ክፍልን ይመልከቱ።

ቅጠሎችን ስለማጽዳት እና ለክረምት የአየር ሁኔታ መዘጋጀትን በተመለከተ ጥቂት ሃሳቦችን ለማግኘት የእኛን SDOT Blog: ይመልከቱ ቅጠሎቹ እየወደቁ ነውና እና መኸር በይፋ እዚህ ነው! የእግረኛ መንገዶቻችንን ማጽዳት እና ለክረምት አየር ሁኔታ መዘጋጀት የምንጀምርበት ጊዜ ነው እና የሲያትል Neighborhood Greenways blog: በደቡብ ሲያትል ውስጥ በጎ ፈቃደኞች የእግረኛ መንገድ እና የብስክሌት መስመሮችን ያጸዳሉ: በደቡብ ሲያትል ውስጥ በጎ ፈቃደኞች የእግረኛ መንገድ እና የብስክሌት መስመሮችን ያጸዳሉ። የኋለኛው መጣጥፍ ከRainier Valley Greenways-Safe Streets እና Beacon Hill Safe Streets በጎ ፍቃደኞች እንዴት ፍርስራሾችን እና ተትረፍርፎ የበቀለውን ወይን ከእግረኛ መንገድ ለማስወገድ፣ የውሃ ማፍሰሻዎችን ያፀዳዱ እና ርጋፊዎችን ከኩርባ መወጣጫ ያፅዱ እና የብስክሌት መስመሮችን በበርካታ ቦታዎች እንዴት እንደሚያጸዱ ይሸፍናል።

በረዶን እና ጠጣር በረዶን ማጽዳት

በረዶ በሚጥልበት ጊዜ በከተማው ውስጥ መዘዋወር አስቸጋሪ እና በተሽከርካሪ ጎማ የሚነዱትን ሲጠቀሙ እንዲያውም የባሰ የበለጠ ፈታኝ ነው። በንብረትዎ ፊት ለፊት በረዶን በአካፋ በማንሳት፣ ለሁሉም ሰው የመዳረሻ ችግሮችን ለመቀነስ ማገዝ ይችላሉ። በረዶን በአካፋ ማንሳትን እና መድረሻን ስለመጠበቅ ከዚህ በታች ያለውን ቪዲዮ ለማዘጋጀት ከበመብቶች ላይ የተመሰረተ (Rooted in Rights) ጋር ሠርተናል።  

የክረምት የአየር ሁኔታ ምላሽ

የእግረኛ መንገድ ምርምር ካርታዎች

የእግረኛ መንገድ ምርምር እና የጥገና ተግባራት (Maintenance Activities) ድህር መተግበሪያዎች ከሲያትል ተደራሽነት መስመር እቅድ አውጪ እና ከሲያትል የመጓጓዣ መምሪያ (SDOT) ንብረቶች ካርታ ጋር በይነተገናኝ ካርታዎች ገጻችን ላይ ይገኛሉ። ለዚህ መመሪያ የበለጠ መረጃ ወደ የእግረኛ መንገድ ጉዳዮች ምርምር (Researching Sidewalk Issues) ክፍል ይሂዱ።  

ስለ ንብረቱ ውሂብ የበለጠ ለማወቅ ከፈለጉ፣ የእራስዎን ካርታዎች ይፍጠሩ፣ ወይም ጋር በተጨማሪ በውሂቡ መስተጋብር ለመለዋወጥ የእኛን GIS Open Data Portal ይመልከቱ።

ስለእነዚህ ካርታዎች ጥያቄዎች ካልዎት ወይም የውሂብ ስህተቶችን ካገኙ፣ በ SDOTAssets@seattle.gov ከአድራሻ እና የንብረት መታወቂያ ጋር ከተሳሳተው ወይም ከጎደለው መረጃ ጋር ያግኙን።

የእግረኛ መንገድ መተካት

የሲያትል ማዘጋጃ ቤት ህግ (SMC), አርእስት 15 የንብረት ባለቤቶች ከንብረታቸው አጠገብ ያለውን የእግረኛ መንገድ ለህዝብ ጉዞ ዓላማዎች ተስማሚ እና ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ይጠይቃል። ከታች ያሉት ጥገና የሚያስፈልጋቸው የእግረኛ መንገዶች ምሳሌዎች ናቸው።

በጐን እግረኛ መንገዱ ውስጥ ከመንገድ ዛፍ አጠገብ ያለው የእግረኛ መንገድ መሰንጠቅ እና የከፍታ ልዩነት ያሳያል። ወደላይ ቀጥ ያለ የእግረኛ መንገድ ስንጥቅ። ትይዩ ቀጥ ያለ የእግረኛ መንገድ ስንጥቅ።

የእግረኛ መንገዱ የተሰነጠቀ ነው።

የእግረኛ መንገድ ከፍ ማድረግ የጎደለው የእግረኛ መንገድ ክፍተት በነጭ ቀለም የተቀባ። ከመሬት አቀማመጥ ጋር የተገጣጠሙ ስንጥቆች እና ክፍተቶች ያሉት የእግረኛ መንገድ እየተበላሸ ነው።

በእግረኛ መንገድ ውስጥ የተበላሸ ወይም ሌሎች ክፍተቶች አሉ።

በእግረኛ ግፊት መንቀሳቀስ የሚችል አንድ ንጣፍ ከግራጫ እና ሮዝ ንጣፎች የተሰራ የእግረኛ መንገድ። ከመሬት ገጽታ፣ ከቅጠሎች እና ከጎዳና ዛፍ አጠገብ የእግረኛ መንገድ ከብዙ የተገለሉ ተዳፋት ችግሮች ጋር። የእግረኛ መንገድ ከገለልተኛ ተዳፋት ጋር ውሃ ወደ ኩሬ የሚያደርስ።

ማንኛውም በተለመደው የእግር ግፊት ሊንቀሳቀስ የሚችል የእግረኛ መንገድ ክፍል ወይም ደረጃው ወይም የእግረኛ መንገዱ ተዳፋት ለአስተማማኝ ለእግረኛ መተላለፊያ ስጋት ይፈጥራል።

ፈቃድ እንዴት ማግኘት እንደሚቻል

የእግረኛውን መንገድ ከመጠገን በፊት፣ ፈቃድ ያስፈልጋል። ይህ የእግረኛ መንገዱ የከተማውን ደረጃዎች የሚያሟላ እና እንደ መገልገያ እና ዛፎች ያሉ መሠረተ ልማቶች መጠበቃቸውን ያረጋግጣል። ለንብረት ባለቤቶች፣ ለሥራ ተቋራጭ ግብዓቶች፣ የእግረኛ መንገድ ጥገና እና የዛፍ መመሪያ፣ እና ማጣቀሻዎች መረጃን የሚሸፍን የ2208 ደንበኛ ድጋፍ ማስታወሻን፣ ይመልከቱ። የእግረኛ መንገድ ንድፍ መመሪያ በመንገዶች የሥዕላዊ መግለጫ የንድፍ ደረጃዎች ምዕራፍ 3.2 ቀርቧል። ስለ ዛፍ የማስተካከል ቁርጥ እና ፈቃዶች የበለጠ መረጃ ለማግኘት የዚህን መመሪያ የዛፍ እንክብካኬ ክፍል ይመልከቱ።

የሥራ ተቋራጭ ለመቅጠር ጎረቤቶችዎን መቀላቀል ወጪ ቆጣቢ እና የእግረኛ መንገዶችን ለመጠገን ውጤታማ መንገድ ሊሆን ይችላል። የንብረት ባለቤቶች በሺዎች የሚቆጠር ዶላር መቆጠብ የሚያስችል በተመሳሳይ ፍቃድ ከቤታቸው ፊት ለፊት ያሉትን የእግረኛ መንገዶችን ለመተካት፣ ከአንድ የሥራ ተቋራጭ ጋር በጋራ መስራት ይችላሉ።

የግንባታ መዳረሻ

በግንባታ ወቅት የእግረኛ መንገድን መዳረሻ ለመጠበቅ አንዳንድ አጋዥ መንገዶች አሉ። ከጠቋሚ ምልክቶች እና ፍርስራሾች የፀዱ መተላለፊያዎችን ማቅረብ፣ ጠንካራ ማገጃዎችን መጠቀም፣ መወጣጫዎችን ማካተት እና የግንባታ አጥርን ማጣራት ለመዳረሻ የሚሆን በቂ ስፋት እንደሚሰጥ ያረጋግጡ።

እንደ ከታች እንደሚታየው እንደ ታጣፊ ሰሌዳዎች ያሉ ጊዜያዊ እንቅፋቶች፣ በጎማ የሚዘወሩ ተሽከርካሪ ውስጥ ያሉ ሰዎች የእግረኛ መንገድን እንዳይደርሱ ያደርጋቸዋል። በሥራ ቀጠኖች ዙሪያ የእግረኞች ተንቀሳቃሽነት ላይ የበለጠ መረጃ ለማግኘት የዳይሬክተሩ ደንብ 10-2015ን ይመልከቱ ።

ይህ የእግረኛ መንገድ በጊዜያዊ የማቆም አይቻልም A የመቃን ምልክት ታግዷል።
 
ይህ ቪዲዮ በመንገድ ባለድርሻ መብት ላይ የሚሰሩ ሰዎችን መዳረሻን ስለመጠበቅ አስፈላጊነት ያስተምራል። ስለመንገድ ስለመንገድ ባለድርሻ መብት (ROW) ግንባታ በድረ-ገጻችን ላይ የበለጠ ይወቁ።

የፍሳሽ ማስወገጃዎችዎን እና የጎን የፍሳሽ ማስወገጃዎችዎን መንከባከብ

ስለ የፍሳሽ ማስወገጃ ቧንቧ እንክብካቤ እና ስለችግርመፍቻ መፈለግ የበለጠ ለማወቅ የሲያትል የህዝብ መገልገያ የጎን የፍሳሽ ማስወገጃ መረጃ እና ሃላፊነቶች ድህረ ገጽን ይጎብኙ። በፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓቱ ውስጥ ያሉትን መዘጋቶች እና ምትኬዎችን ለመቀነስ እነዚህን አጋዥ መመሪያዎች ይመልከቱ: ምን ታጥቦ መለቀቅ እንዳለብት፣ እና ስብ፣ ዘይቶች እና ቅባት

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሀይል መሙላት

በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ላይ መዋዕለ ንዋይ እያደረጉ ነው እና ከቤትዎ እስከ ቤትዎ ፊት ለፊት ያለው መንገድ ድረስ ሀይል ለመሙላት እንዲችሉ ማረጋገጥ ይፈልጋሉ? የመሰናከል ችግር እንዳይፈጥር በእግረኛ መንገድ ላይ የኃይል መሙያ ገመድ እንዴት እንደሚገጠም መመሪያ የሚሰጥ ለመኖሪያ ቤት አገልግሎት የሚሆን የደንበኛ ድጋፍ ማስታወሻ (CAM 2119) እነሆ። 

የእግረኛ መንገድ ካፌ መመሪያዎች

ስለ የእግረኛ መንገድ ካፌ መመሪያዎች እና እንደ ጃንጥላ፣ የመቃን ምልክቶች፣ ጠረጴዛዎች እና ወንበሮች ያሉ መሰናክሎች በዚህ ቪዲዮ ውስጥ የበለጠ ይረዱ።

የዝናብ ውሃ ብክለትን በሚከላከሉበት ጊዜ የፍሳሽ ማስወገጃዎችዎን እና የጎን የፍሳሽ ማስወገጃዎችዎን መንከባከብ

ስለ የፍሳሽ ማስወገጃ ቧንቧ እንክብካቤ እና ስለችግርመፍቻ መፈለግ የበለጠ ለማወቅ የሲያትል የህዝብ መገልገያ የጎን የፍሳሽ ማስወገጃ መረጃ እና ሃላፊነቶች ድህረ ገጽን ይጎብኙ። በፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓቱ ውስጥ ያሉትን መዘጋቶች እና ምትኬዎችን ለመቀነስ እነዚህን አጋዥ መመሪያዎች ይመልከቱ: ምን ታጥቦ መለቀቅ እንዳለብት፣ እና ስብ፣ ዘይቶች እና ቅባት። ንግዶች ነፃ የብክለት መከላከያ የሚፈስ ውሃ ጥቅል (Spill Kits) እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ እና የዝናብ ውሃ ደንቦችን ለማክበር ስለማቀድ እዚህ ተጨማሪ መረጃ አለ።

የእግረኛ መንገድ ጉዳዮችን ጥናትዊ ምርመራ

የእግረኛ መንገድ ጥናትዊ ምርመራ እና የጥገና ተግባራት በድህር መተግበሪያዎች ከሲያትል ተደራሽነት መስመር እቅድ አውጪ እና ከሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT) ንብረቶች ካርታ ጋር በይነተገናኝ ካርታዎች ገጻችን ላይ ይገኛሉ። ስለ ንብረቱ ውሂብ የበለጠ ለማወቅ ከፈለጉ፣ የእራስዎን ካርታዎች ይፍጠሩ፣ ወይም ጋር በተጨማሪ በውሂቡ መስተጋብር ለመለዋወጥ የእኛን GIS Open Data Portal ይመልከቱ።

ስለእነዚህ ካርታዎች ጥያቄዎች ካልዎት ወይም የውሂብ ስህተቶችን ካገኙ፣ የአካባቢ እና የንብረት መለያ መታወቂያ ከተሳሳተ ወይም የጎደለው መረጃ ጋር በ SDOTAssets@seattle.gov ያግኙን።

የእግረኛ መንገድ የጥናት ምርምር መተግበሪያ

 
የእግረኛ መንገድ ምርምር ካርታው አላማ ሰዎች የእግረኛ መንገድ ምልከታዎችን እና ተዛማጅ መረጃዎችን እንደ የመንገድ ዛፎች፣ የጎን ፍሳሽ ማስወገጃዎች፣ የውሃ መስመሮች፣ እና የንብረት ባለቤትነት ላይ ምርምር የሚያደርጉበትን መድረክ መፍጠር ነው። 
 
በመተግበሪያው የላይኛው ግራ በኩል የማጉያ መነጽር ያለው የፍለጋ አሞሌ አለ።  አድራሻዎችን፣ የንብረት መታወቂያዎችን፣ ከ ፈልጉ፣ አስተካክሉ (Find It, Fix It) መተግበሪያ መጠየቂያዎችን የውጭ ማመሳከሪያ ቁጥሮችን፣ ወይም በሲያትል ከተማ ድንበሮች ውስጥ ያሉ ቦታዎችን ያስገቡ እና ካርታዎቹ ወደዚያ ቦታ/ አድራሻ ያስሳሉ። ከላይ በግራ በኩል ያሉት የመደመር እና የመቀነስ አዶዎች በማያ ገጹ ላይ ለማጉላት እና ለማሳነስ ያገለግላሉ። በብቅ-ባይ ውስጥ የባህሪ መረጃን ለማሳየት በይነተገናኝ ካርታዎች ውስጥ ያሉትን ባህሪያት ጠቅ ያድርጉ። ውሂቡ ደግሞ በእያንዳንዱ ካርታ ግርጌ ላይ ባለው የባህሪ ሠንጠረዥ ውስጥም ሊታይ ይችላል።  በሰንጠረዡ ውስጥ ያለው ውሂብ "አማራጮች" (“Options”) ተቆልቋይ ምናሌን በመጠቀም ወደ ኤክሴል (excel) የተመን ሉህ መላክ ይቻላል። ስለ መግብር (ከዚህ በታች የሚታየው) መተግበሪያውን እንዴት ማሰስ እንደሚቻል መመሪያ ይሰጣል።

ስለ መግብር አዶ

በእግረኛ መንገድ ምርምር መተግበሪያ ውስጥ እንዲበሩ/ሠሩ እና ሊጠፉ የሚችሉ በርካታ ንብርብሮች አሉ።

 • ዛፎች ንብርብር በዛፍ ባለቤትነት ይመሰላል። የበለጠ መረጃ ስለ ዝርያዎቹ ዓይነቶች፣ መጠኖች እና በብቅ ባዩ ምናሌ ዝርዝዝር ውስጥ ዛፉን ለመጨረሻ ጊዜ ስለጎበኘንበት ወቅት ለማግኘት የተለያዩ የቀለም ክበቦችን ጠቅ ያድርጉ። 
 • የእግረኛ መንገድ ምልከታ ውሂብ በምልከታ አይነት ይመሰላል።  ስለዚያ ስለተለየ እንደ የፍተሻ ቀን፣ የምልከታ አይነት እና የቅርቡ ጊዜ የመሬት ክልል መታወቂያ ቁጥር ያሉ መረጃዎችን የምልከታ ውሂብ ለማየት በነጥቦቹ ላይ ጠቅ ያድርጉ።  በሠራተኞቻችን ብድኖች ወይም በካፒታል፣ በግል እና በአገልግሎት ፕሮጀክቶች የእግረኛ መንገድ ጥገናዎች መከናወናቸውን ሲያታውቁን የየምልከታ ውሂቡን እናርማለን ወይም እናዘምነዋለን።
 • ያልተሻሻሉ የእግረኛ መንገዶች የእግረኛ መንገዶች የጎደሉባቸውን ክፍተቶች ያሳያል። 
 • የእግረኛ መንገድ ንብረት ውሂብ በሁኔታ ይመሰላል።  ከ2017 ጀምሮ የውሂብ መረጃው እንዴት እንደተሰበሰበ የበለጠ ለማወቅ፣ በዚህ የእግረኛ መንገድ መመሪያ ውስጥ የእግረኛ መንገድ ግምገማ እና ሁኔታዎች ታሪክ ካርታን ይመልከቱ።
 • የኩርባ መወጣጫዎች (Curb Ramps) በሁኔታ እና በምድብ ይመሰላሉ።
 • የጎን የፍሳሽ ማስወገጃዎች እና የጎን በኩል እና የውሃ አገልግሎቶች SPU እና የግል ንብርብሮች ከመሬት በታች የውሃ እና የፍሳሽ አገልግሎቶችን ያሳያሉ።  

በየሳምንቱ ከሜታዳታ (metadata) ጋር የሚሻሻሉት እነዚህ ንብርብሮች በከተማው ክፍት የውሂብ ድህረ ገጽ ላይ በሰንጠረዥ CSV ቅርጸት፣ ጽሑፍን መሰረት ባደረገ የጥናት ምርምር መልኩ በካርታ ስራ ላይ ከሚውሉ ሌሎች ቅርጸቶች ጋር ማግኘት ይችላሉ። በእግረኛ መንገድ የጥገና ፕሮግራማችን ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የእኛን የጥገና ታሪክ ካርታችንን ይመልከቱ።
 
የእግረኛ መንገድዎን አስተካክለዋል? የእግረኛ መንገድን መረጃ ለመለየት የእግረኛ መንገድ የጥናት ምርምር ካርታን ይጠቀሙ እና ከዚያም የንብረት አድራሻውን፣ የምልከታ መታወቂያውን፣ የፍቃድ ቁጥርን፣ እና ጥገና የተደረገለትን የእግረኛ መንገዱን ያካትቱ ምስሎችን ወደ SDOTAssets@seattle.gov ኢሜይል ይላኩልን።  

የእግረኛ መንገድ የጥገና ተግባራት/ ክስተቶች ማመልከቻ

የጥገና ተግባራት/ ክስተቶች ካርታ አላማ የእግረኛ መንገድ የጥገና ስራዎችን ክስተቶች ለማየት እና የጥናታዊ ምርምር መድረክን ማቅረብ ነው።

በመተግበሪያው የላይኛው ግራ በኩል የማጉያ መነጽር ያለው የፍለጋ አሞሌ አለ።  አድራሻዎችን፣ የንብረት መታወቂያዎችን፣ ከ ፈልጉ፣ አስተካክሉ (Find It, Fix It) መተግበሪያ መጠየቂያዎችን የውጭ ማመሳከሪያ ቁጥሮችን፣ ወይም በሲያትል ከተማ ድንበሮች ውስጥ ያሉ ቦታዎችን ያስገቡ እና ካርታዎቹ ወደዚያ ቦታ/ አድራሻ ያስሳሉ። ከላይ በግራ በኩል ያሉት የመደመር እና የመቀነስ አዶዎች በማያ ገጹ ላይ ለማጉላት እና ለማሳነስ ያገለግላሉ። በብቅ-ባይ ውስጥ የባህሪ መረጃን ለማሳየት በይነተገናኝ ካርታዎች ውስጥ ያሉትን ባህሪያት ጠቅ ያድርጉ። ውሂቡ ደግሞ በእያንዳንዱ ካርታ ግርጌ ላይ ባለው የባህሪ ሠንጠረዥ ውስጥም ሊታይ ይችላል።  በሰንጠረዡ ውስጥ ያለው ውሂብ "አማራጮች" (“Options”) ተቆልቋይ ምናሌን በመጠቀም ወደ ኤክሴል (excel) የተመን ሉህ መላክ ይቻላል። ስለ መግብር (ከዚህ በታች የሚታየው) መተግበሪያውን እንዴት ማሰስ እንደሚቻል መመሪያ ይሰጣል።

ስለ መግብር አዶ

በመተግበሪያው ውስጥ ሊበሩ/ እንዲሠሩ ሊደረጉ እና ሊጠፉ የሚችሉ በርካታ የስራ ቅደም ተከተል ንብርብሮች አሉ።

 • የእግረኛ መንገዱ በግምት ከ1.75 ኢንች ያልበለጠ ከፍ ከተደረገ፣ ደረጃውን የጠበቀ ልዩነቱን የተደላደለ ንጣፍ ወለል ለመፍጠር ሰያፍ መቁረጥ ወይም መፍጨት እንችላለን። ሰያፍ ቁርጦች በተፈጥሮ ውስጥ ጊዜያዊ ናቸው እና እነዚህን አካባቢዎች ለማለዘብ ይረዳሉ።
 • የእግረኛ መንገድ ስንጥቆች እና ከፍታዎች ላይ የአስፓልት ሽብልቆችን እናስቀምጣለን። እነዚህ "ሽብልቆች" በተፈጥሯቸው ጊዜያዊ ናቸው እና የረጅም ጊዜ ጥገና ከመደረጉ በፊት የተጎዳውን አካባቢ ለእግረኞች ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ ይረዳሉ። 
 • የእግረኛ መንገድ እና የኩርባ ጥገናዎች የበለጠ ቋሚ ናቸው እና በተለምዶ ሙሉውን የልበዳውን መተካት ወይም የኩርባ ግንባታን ይጠይቃል። 

እነዚህ ንብርብሮች፣ ከሜታዳታ (metadata) ጋር፣ በከተማው ክፍት የውሂብ ድህረ ገጽ ላይ በሰንጠረዥ CSV ቅርጸት፣ ጽሑፍን መሰረት ባደረገ የጥናት ምርምር መልኩ በካርታ ስራ ላይ ከሚውሉ ሌሎች ቅርጸቶች ጋር ሊደረስባቸው ይችላሉ።

በእግረኛ መንገድ የጥገና ፕሮግራማችን ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የእኛን የጥገና ታሪክ ካርታችንን ይመልከቱ።  

የዛፍ እንክብካቤ/ ጥገና

ከ 2 ጫማዎች የክብ አጋማሽ መስመር በላይ የሆኑትን የዛፍ ሥሮችን እና እግሮችን ከመከርከምዎ በፊት ወይም ከ 15% በላይ የሚሆነውን ቅጠሉን የሚሸከምበት ማንኛውንም ዋናውን ክርከማ ከማድረግዎ አስቀድሞ ፈቃድን እና የሲያትል ማመላለሻ መምሪያ (SDOT) የዛፍ ማለሙያ መከርከሙ በዛፉ ጤና እና በሕዝብ ደህንነት ላይ ሊያመጣ የሚችለውን ተጽዕኖ እንዲገመገም ማመቻቸት አለብዎት። የእኛን የመንገድ ዛፍ ፈቃዶች ድህረ ገጽን ይጎብኙ ወይም በ 206-684-TREE (8733) ይደውሉ።  
 
የእግረኛ መንገድ ጥናታዊ ምርመራ እና የሲያትል ማመላለሻ መምሪያ (SDOT) ንብረቶች ካርታ የድህር መተግበሪያዎቻችን በይነተገናኝ ካርታዎች ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ካርታዎች በሲያትል የመንገድ ዛፎች ላይ የባለቤትነት መረጃን ያካትታሉ። የበለጠ መረጃ ስለ ዝርያዎቹ ዓይነቶች፣ መጠኖች እና በብቅ ባዩ ምናሌ ዝርዝዝር ውስጥ ዛፉን ለመጨረሻ ጊዜ ስለጎበኘንበት ወቅት ለማግኘት የተለያዩ የቀለም ክበቦችን ጠቅ ያድርጉ። በአድራሻ ወይም በቦታ ላይ ወይም ከታች በቀኝ በኩል ያሉትን የመደመር እና የመቀነስ አዶዎችን ለመፈለግ ከላይ በስክሪኑ ወድውስጥ እና ወድውጭ ለማሳደግ እና ለማሳነስ ሽው ማድረግ በግራ በኩል ያለውን የማጉያ ብርጭቆውን ይጠቀሙ።  
 
የመንገድ ዛፉ ውሂብ በከተማው ክፍት ውሂብ ጣቢያ ላይ በሰንጠረዥ CSV ቅርጸት፣ ጽሑፍን መሰረት ባደረገ መልኩ ጥናታዊ ምርምር ማድረግ፣ የካርታ ስራ መተግበሪያዎች ውስጥ ከሚውሉ ሌሎች ቅርጸቶች ጋር ማግኘት ይቻላል።

ስለ የሲያትል መንገድ ዛፎች እና የከተማ አጐበሮች የበለጠ ለማወቅ የእኛን የመንገድ ዛፍ የታሪክ ካርታ (StoryMap) ይጎብኙ። ስለ የፍሳሽ ማስወገጃ ቧንቧ እንክብካቤ እና ስለዛፍ ሥር ችግርመፍቻ ፍለጋ የበለጠውን ለማወቅ የሲያትል የህዝብ መገልገያ የጎን የፍሳሽ ማስወገጃ መረጃ እና ሃላፊነቶች ድህረ ገጽን ይጎብኙ። በፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓቱ ውስጥ ያሉትን መዘጋቶች እና ምትኬዎችን ለመቀነስ እነዚህን አጋዥ መመሪያዎች ይመልከቱ: ምን ታጥቦ መለቀቅ እንዳለብት፣ እና ስብ፣ ዘይቶች እና ቅባት

ከተማው ለእግረኛ መንገድ ጥገና እና ተከላ እንዴት ቅድሚያ እንደሚሰጥ

የእግረኛ መንገድ ጥገና

የጥገና/መንከባከቢያ አካሄዳችን የእግረኛ መንገድ ጥገናን እና የቦታ አያያዝን ከሥነ-መልክአ-ምድራዊ እና ፍትሃዊ እኩልነት ምክንያቶች ጋር በተንቀሳቃሽነት ተፅእኖዎች፣ ስጋት፣ ወጪ፣ እና አጠቃቀም ላይ መስረት በማድረግ ቅድሚያ ይሰጣል። እንዲሁም ጥገና ከሚያስፈልጋቸው የእግረኛ መንገዶች አጠገብ ካሉ ሌሎች የካፒታል ፕሮጀክቶች ጋር እንሰራለን። ግቡ የተሰጠውን የተገደበ የጥገና በጀት በመጠቀም ለህብረተሰቡ ከፍተኛ ዋጋ ያለውን መስጠት ነው።  

እያንዳንዱ የእግረኛ መንገድ በአራት የተለያዩ ምድቦች ነጥብ ተሰጥቶታል: አደጋ፣ የተንቀሳቃሽነት እክል፣ ወጪ እና አጠቃቀም። ለእግረኛ መንገድ ተጠቃሚዎች የአደጋው ስጋት ሊያስከትል ከሚችለው ጉዳት ያመዝናል። የመራመድ ችሎታ ላላቸው ተጠቃሚዎች የተንቀሳቃሽነት ጉዳት ችግሩን ይይዛል። የእግረኛ መንገዱን ሁኔታ ለማስተካከል ያለውን አቅም እንገምታለን። የአጠቃቀም ውጤት ነጥብ የእግረኛ መንገድ ተጠቃሚዎችን ቁጥር እና አላማ ይገመታል።  አስፈላጊ እና ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው ተቋማት አጠገብ ያሉት የእግረኛ መንገዶች፣ የመንግስት ተቋማት (የማህበረሰብ ማእከላት፣ ቤተ-መጻህፍት፣ መናፈሻዎች፣ ማህበራዊ አገልግሎቶች)፣ የጤና አገልግሎቶች/ሆስፒታሎች፣ የሕዝብ መጓጓዣ ጣቢያዎች እና ኮሪደሮች፣ የቅጥር ማዕከላት፣ ትምህርት ቤቶች እና የአረጋውያን/የአካል ጉዳተኞች መኖሪያ ቤቶችን ያካትታሉ።   

ለበለጠ መረጃ የእግረኛ መንገድ ጥገና ፕሮግራምን፣ የጥገና ፕሮግራምን እና የ2020 የዋሽንግተን ኢቫንስ ትምህርት ቤት በሲያትል ዘገባ ውስጥ የእግረኛ መንገድ ጥገና የፖሊሲ ምክሮችን ይጎብኙ።

በሂደት ውስጥ ላለ ስራ እና ለተዘጉ የስራ ትዕዛዞች የእኛን የእግረኛ መንገድ የጥገና ተግባራት/ክስተቶች የድር መተግበሪያን ይመልከቱ።

አዳዲስ የእግረኛ መንገዶች እና መራመጃ መንገድ

ከእያንዳንዱ የልማት መንገዶች፣ የፍሳሽ ማስወገጃዎች እና የውሃ አገልግሎት ጋር በሲያትል ውስጥ ያሉት አብዛኛዎቹ የእግረኛ መንገዶች የተገነቡት መጀመሪያ በእያንዳንዱ አካባቢ በንዑስ ተከፋፍሎ እና ክፍያቸው ከአካባቢ የማሻሻያ ወረዳዎች (LIDs) በነበረበት ወቅት ነው።  የግንባታ አልሚዎች ሁሉ አልነበሩም የእግረኛ መንገዶችን መገንባት የመረጡት።  በ1950ዎቹ ከከተማዋ ጋር ተቆራኝተው የነበሩ አካባቢዎች የእግረኛ መንገዶችን አስፈላጊነት ያልመረጡትን ያልተካተተ የኪንግ ካውንቲ የደረጃ መመዘኛዎችን ተጠቅመዋል።   
 
የእግረኛ መንገድ ልማት ፕሮግራም በእግረኞች ማስተር ፕላን (PMP) ውስጥ የወጣውን የቅድሚያ መስፈርቶችን ይጠቀማል።

 • በሲያትል ውስጥ ለአዳዲስ የእግረኛ መንገዶች የገንዘብ ድጋፍ ከተለያዩ ምንጮች የሚመጣ ሲሆን የሚከተሉትን ይጨምራል:
 • የእግረኛ መንገድ ልማት ፕሮግራም
 • ወደ ትምህርት ቤት ደህንነቱ የተጠበቀ መስመሮች (SRTS) ፕሮግራም
 • ለሰፈር መንገድ የተዋጣ የድጋፍ ገንዘብ
 • የካፒታል ፕሮጀክቶች
 • የትምህርት ቤት ፍጥነት ካሜራ መዋጮዎች
 • የግል ልማት
 • ሌሎች ተወካይ ድርጅቶች  

በወደ ትምህርት ቤት አስተማማኝ መስመሮች ፕሮግራም በኩል የሚደረጉ የገንዘብ ድጋፍ ፕሮጀክቶች በተመሳሳይ መንገድ ቅድሚያ ተሰጥቷቸዋል። ለሰፈር መንገድ የተዋጣ የድጋፍ ገንዘብ ፕሮግራም ማመልከቻዎች በእያንዳንዱ ምክር ቤት ወረዳ ውስጥ ባሉ በማህበረሰቡ ቅድሚያ ተሰጥቷቸዋል፣ ከዚያም በማህበረሰብ አባላት ድምጽ ተሰጥቶባቸዋል። የመጨረሻው የፕሮጀክት ምርጫ የሚከናወነው በMove Seattle Levy Oversight Committee በኩል ነው።

የእግረኛ መንገዶችን የሚነኩ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ወደ ፕሮጄክታችን እና የግንባታ ማስተባበሪያ ካርታችን ተጨምረዋል።
 
ለበለጠ መረጃ የእኛን አዳዲስ የእግረኛ መንገዶች እና የእግር መንገዶች ታሪክ ካርታ (StoryMap) ይመልከቱ።  

መሳተፍ

ቦርድ/ምክር ቤት ለመቀላቀል ቢፈልጉ፣ በአካባቢያችሁ ያሉትን እፅዋት ለማፅዳት፣ ወይም የእግረኛ መንገድዎን ከጠገኑ ሊያሳውቁን ከፈለጉ ሲያትል ለመሳተፍ ጥቂት ምርጥ መንገዶች አሏት።

የሲያትል የእግረኛ አማካሪ ቦርድን ይቀላቀሉ ወይም ስብሰባዎችን ይሳተፉ

https://www.seattle.gov/seattle-pedestrian-advisory-board 

ከሲያትል የማመላለሻ መምሪያ ጋር ይሳተፉ

https://www.seattle.gov/transportation/about-us/get-involved 

ዕፅዋትን ለማጽዳት የበጎ ፈቃደኞች ጥረቶች

Adopt-a-Street ወይም Spring Clean በመሳተፍ የሲያትል መንገዶችን እና የእግረኛ መንገዶችን ከቆሻሻ ነጻ ያቆዩ።

Adopt-a-Street የሲያትል ሥረ-መሰረታዊ ቆሻሻን የማስወገድ ፕሮግራም ነው። በመቶዎች የሚቆጠሩ ማይሎችን የሲያትል ከተማ መንገዶችን እና የእግረኛ መንገዶችን የሚያጸዱ በሺዎች የሚቆጠሩ በጎ ፈቃደኞችን ይቀላቀሉ።

ቅጠሎችን ስለማጽዳት እና ለክረምት የአየር ሁኔታ ለመዘጋጀት ጥቂት ሃሳቦችን ለማግኘት የእኛን SDOT ብሎግ/ጦማር ይመልከቱ: ቅጠሎቹ እየወደቁ እና መኸር በይፋ እዚህ ነው! የእግረኛ መንገዶቻችንን ማጽዳት እና ለክረምት የአየር ሁኔታ እና የሲያትል ግሪንዌይ ጦማር በጎ ፈቃደኞች በደቡብ ሲያትል የእግረኛ መንገዶችን እና የብስክሌት መስመሮችን ግልጥ ለማድረግ መዘጋጀት የምንጀምርበት ጊዜ ነው። የኋለኛው መጣጥፍ ከRainier Valley Greenways-Safe Streets እና Beacon Hill Safe Streets በጎ ፍቃደኞች እንዴት ፍርስራሾችን እና ተትረፍርፎ የበቀለውን ወይን ከእግረኛ መንገድ ለማስወገድ፣ የውሃ ማፍሰሻዎችን ያፀዳዱ እና ርጋፊዎችን ከኩርባ መወጣጫ ያፅዱ እና የብስክሌት መስመሮችን በበርካታ ቦታዎች እንዴት እንደሚያጸዱ ይሸፍናል።

የእግረኛ መንገድዎን ሲጠግኑ ያሳውቁን

የእግረኛ መንገድዎን አስተካክለዋል? የእግረኛ መንገድን መረጃ ለመለየት የእግረኛ መንገድ የጥናት ምርምር ካርታን ይጠቀሙ እና ከዚያም የንብረት አድራሻውን፣ የምልከታ መታወቂያውን፣ የፍቃድ ቁጥርን፣ እና ጥገና የተደረገለትን የእግረኛ መንገዱን ያካትቱ ምስሎችን ወደ SDOTAssets@seattle.gov ኢሜይል ይላኩልን።

የእግረኛ መንገዶችን እና ማሻሻያዎች እንዴት እንደሚጠየቁ

በሲያትል የእግረኛ አማካሪ ቦርድ ውስጥ ከመሳተፍ በተጨማሪ፣ የሲያትል ከተማ የእግረኛ መንገድ አውታረ መረብ እድሎችን ለመለየት ከማህበረሰቦቻችን ጋር አብረው የሚሰሩ በርካታ ፕሮግራሞች አሏት: 

የእግረኛ መንገድ ታሪክ እና የንብረት ሁኔታዎች

የኛ የ2017 የእግረኛ መንገድ ግምገማችን የስርዓት-ሁሉን-አቀፍ የጥገናዎች ፍላጎቶችን ለይቶ ለማወቅ በእግረኛ መንገዶቻችን ላይ ያሉ ችግሮችን ተመልክቷል፤ ከኋላ ጊዜ ጀምሮ ጥገናዎች የገንዘብ ድጋፍን እንዲያገኙ መክሯል፤ የእግረኛ መንገድ ጥገና ፍላጎቶችን ግንዛቤ እንዲያድግ አድርጓል፤ የእግረኛ መንገድ ፍተሻ እና የማስፈጸሚያ መርሃ ግብርን አውጥቷል፤ ለይገባኛል ጥያቄዎች እና የሙግት ድጋፍ ጥረቶች ምላሽ ሰጥቷል፤ የገንዘብ ድጋፍ ዕድሎችን ተጠቅሞበቸዋል፤ እና ሃላፊነታቸውን ለንብረት ባለቤቶች አሳውቋል። 

ግምገማውን ተከትሎ የእግረኛ መንገድ ጥገና በጀት ጨምሯል፣ እና ምልከታዎችን ሥራ ላይ እንዲውሉ ለማድረግ ለከተማ አቀፍ አቀራረብ ቅድሚያ መስጠት ተጀምሯል። እድሳት የሚያስፈልጋቸውን የእግረኛ መንገዶች አጠገብ ያሉ ሌሎች የካፒታል ፕሮጀክቶችን ጥቅም ላይ እያዋልን፣ የጥገና አካሄዳችን አሁን በእግረኛ መንገድ ጥገና እና በተንቀሳቃሽነት ተፅእኖዎች፣ በአደጋ፣ በዋጋ፣ እና በአጠቃቀም ላይ በመመርኮዝ የእግረኛ መንገድ ጥገና እና ቅነሳን ከሥነ-መልክአ-ምድራዊ እና ማህበራዊ የፍትህ እኩልነት ስርጭት ጋር የእኛ የጥገና አካሄድ አሁን ቅድሚያ ይሰጣል። ግቡ የተሰጠውን የተገደበ የጥገና በጀት በመጠቀም ለህብረተሰቡ ከፍተኛ ዋጋ ያለውን መስጠት ነው።

የበለጠ ለማወቅ የእግረኛ መንገድ ግምገማ እና ሁኔታዎች የታሪክ ካርታ (StoryMap) እና የእኩልነት ክፍላችንን ይመልከቱ።

እኩልነት

መጓጓዣ የቀለም ማህበረሰቦችን እና በሁሉም ገቢዎች፣ ችሎታዎች እና ዕድሜዎች ያሉ የሌሎችንም ፍላጎቶችን ሁሉ ማሟላት አለበት። በዘር ፍትሃዊ እኩልነት እና ማህበራዊ ፍትህ ያለው የማመላለሻ ስርዓት ለመገንባት ከማህበረሰቦቻችን ጋር ሽርክና በማዳበርር ላይ ነን።  በጥቁር፣ በአገሬው ተወላጆች እና በቀለም ሰዎች (BIPOC) ማህበረሰቦች ውስጥ ያሉ ታሪካዊ ልዩነቶችን እንዲቀረፍ ለማድረግ የሀብት ምንጮችን ወደ ከሚገባቸው በታች ለተገለገሉ ማህበረሰቦች በመምራት እና ትክክለኛ ተሳትፎን ለመደገፍ እንፈልጋለን።

የቀለም ማህበረሰቦች፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ማህበረሰቦች፣ አዲስ ነዋሪዎች እና ስደተኛ ማህበረሰቦች፣ አካል ጉዳተኞች እና የቤት እጦት ወይም የመኖሪያ ቤት አስተማማኝነት ከሌላቸው ገጠመኞች፣ ብዙውን ጊዜ ቀደም ሲል ቀይ ቀለም ያላቸው ሰፈሮችን፤ ከሌሎች ዘር-ተኮር የሚቀጥሉ ማህበራዊ-ኢኮኖሚያዊ ልዩነቶች መካከል ደህንነቱ የተጠበቀ፣ አካባቢዊ ዘላቂነት የሚኖረው ጥበቃ፣ ተደራሽ እና በተመጣጣኝ ዋጋ የመጓጓዣ እና የመኖሪያ ቤት እንቅፋቶች የሚቀጥሉባቸው አካባቢዎች ጨምሮ የመኖር አዝማሚያ አለቸው። 

የደንበኛ ጥያቄዎች ለአዲስ እና በተገቢው ለተያዙ የመዋቅራዊ መሠረተ ልማት ዋና ነጂዎች ሲሆኑ፣ የበለጸጉ የሲያትል ክፍሎች በእነዚህ ታሪካዊ የአገልግሎት ፍትሃዊ እኩልነት እና ያልተመጣጠነ የማህበረሰብ ሀብት ምክንያት የተሻለ ጥራት እና ተጨማሪ ንብረቶች ሊኖራቸው ይችላል። የማመላለሻ ስርዓታችን የሁሉንም ሰው ፍላጎት የሚያሟላ መሆኑን ማረጋገጥ አለብን።  

ፍትሃዊ እኩልነትን መገምገም ታሪካዊ በሆኑ ምክንያቶች ተጽእኖ የደረሰባቸው፣ በአሁን ጊዜ እና በወደፊቱ ላይ ስላላቸው ሰዎች እና ቦታዎች ወሂብን ይፈልጋል።  እና መረጃችንን መዋቅራዊ የመሠረተ ልማት እና አገልግሎቶች ላይ ያለውን ልዩነት ለመተንተን እና ለመለየት፣ መዋዕለ ንዋዮችን በፍትሃዊ እኩልነት መነፅሮች ለማስቀደም፣ እና የጥገና ሥራዎችን እንቅስቃሴ ዝርጋታ ለማሻሻል እንጠቀማለን።

የእኛ መረጃ የንብረት ሁኔታን፣ ባህሪያትን እና ሌሎች በአካባቢው የፍትሃዊ እኩልነት ትንተና የሚደግፉ በመደበኛነት የዘመኑ መረጃዎችን ያካትታል።  የጥገና እና የመተካት ስልቶችን በበለጠ ፍትሃዊ እኩልነት ባለው መልኩ ለማሰራጨት የንብረት ሁኔታን በጊዜ፣ በአፈጻጸም፣ የአደጋ ስጋት አንድምታ እና አገልግሎት ለመተንተን እንደ አይነት፣ መጠን፣ ዕድሜ፣ ሁኔታ እና የታቀዱ መዋቅራዊ መሠረተ ልማት ያሉ የንብረት ወሂብ ባህሪያትን እንጠቀማለን።  መረጃው የመዋቅራዊ መሠረተ ልማት ሁኔታ ደረጃ አሰጣጡ ዝቅተኛ የሆነበት ነገር ግን የፍትሃዊነት ቅድሚያ ከፍተኛ የሆነባቸውን ቦታዎች ወይም በከተማው ውስጥ ያለፉ ስራዎች እንዴት እንደተሰሩ ያሳያል።

በ2021፣ የከተማው የንብረት/ሂሳብ ተቆጣጣሪ የሲያትልን የእግረኛ መንገድ እንክብካቤ እና ጥገና ፕሮግራምን ገመገመ። የሲያትል የእግረኛ መንገዶችን ለመጠገን እና ለመጠገን ፍትሃዊ እኩልነት መነጽርን እንዴት እንደምንጠቀም የበለጠ ለማወቅ ሪፖርቱን ያንብቡ እና "ከተማዋ የእግረኛ መንገድ ጥገናን እና መስራትን እንዴት ቅድሚያ እንደምትሰጥ" የሚለውን ክፍል ይመልከቱ። ስለ የእግረኛ መንገድ ጥገና ፕሮግራማችን ለበለጠ መረጃ፣ የእኛን የእምክብካቤ ፕሮግራም ታሪክ ካርታ (StoryMap) ይጎብኙ።

ተደራሽነት

እፅዋት እና እንቅፋቶች የእግረኛ መንገድን መድረሻ ከ36 ጫማ ባነሰ ሲገድቡ፣ በጎማ የሚዘወሩ ተሽከርካሪዎችን ለሚጠቀሙ ሰዎች፣ ከተማውን ለመዘዋወር አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል።  የበረዶ እና የበረዶ ጠጠር ክምችት ማለት በጎማ የሚዘወሩ ተሽከርካሪዎችን ለሚጠቀሙ ሰዎች ከዚያም የበለጠ ፈተናዎች ማለት ነው። የእግረኛ መንገድ ተደራሽነትን እና ለሁሉም ተጠቃሚዎች ሁኔታዎችን እንዴት ማሻሻል እንደሚችሉ ላይ ጥቂት የሀብት ምንጮች እና ምሳሌዎች ከዚህ በታች አሉ።

የብስክሌት መጋራት እና የአነስተኛ ሞተር ብስክሌት መጋራት ሰዎች እንዲዘዋወሩ ለመርዳት ጥሩ አማራጮች ናቸው። ነገር ግን፣ በእግረኛ መንገዱ ላይ ሲቀሩ፣ እነዚህ ጊዜያዊ እንቅፋቶች የማየት ችሎታቸዉ ዝቅተኛ ለሆነ ወይም ማየት ለማይችሉ ሰዎች እና እንደ በተሽከርካሪ ወንበሮች ያሉ የተንቀሳቃሽነት መሳሪያዎች ላይ ላሉ ሰዎች ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ። የብስክሌት ወይም የአነስተኛ ሞተር ብስክሌት መጋራትን በሚጠቀሙበት ወቅት፣ ቢያንስ 6 ጫማ የሆነ ከእግረኛ መንገድ ቦታ በመተው እና ብስክሌቱን ወደ ብስክሌት መደርደሪያ ወይም በእግረኛ መንገድ እና በመንገዱ መካከል ባለው ክፍተት ውስጥ በትክክል ማቆምዎን ያረጋግጡ። የህዝብ ማመላለሻ ማቆሚያዎችን፣ የመናፈሻ መቀመጫዎችን፣ የመኪና መውጫ መንገዶችን እና በሮችን አይዝጉ። ትክክል ባልሆነ መንገድ የቆሙ ብስክሌቶችን እና የአነስተኛ ሞተር ብስክሌቶችን ካዩ፣ ለሌሎች የእግረኛ መንገድ ተጠቃሚዎች ከመንገዳቸው ላይ በማንቀሳቀስ/ በማንሳት ወይም ከታች ባሉት ማናቸውም ዘዴዎች ሪፖርት በማድረግ መርዳት ይችላሉ።

የሲያትል ትራንስፖርት መምሪያ (SDOT)ን በ (206) 684-ROAD (7623) ይደውሉ

684-ROAD@seattle.gov ኢሜይል ያድርጉ

አንድ የድህር ቅጽ ይሙሉ

የከተማውን አግኝ፣ አስተካክል (Find It, Fix It) መተግበሪያን ይጠቀሙ

በትክክል እንዴት እና የት ማቆም እንዳለብዎ የበለጠ መረጃ ለማግኘት፣ እዚህ ጠቅ ያድርጉ እና የእኛን ቪዲዮ ይመልከቱ “የብስክሌት መጋራት ማቆሚያ: ትክክለኛውን ነገር ያድርጉ!

ለበለጠ መረጃ፣ የእግረኛ መንገድ ጥገና ፕሮግራምን ይጎብኙ፣ የእግረኛ መንገድ ጥገና ፖሊሲ ሪፖርትን ይመልከቱ፣ እና ስለጎደሉት የእግረኛ መንገዶቻችን እና ፕሮጀክቶቻችን የበለጠ ለማወቅ የእኛን አዲስ የእግረኛ መንገዶች እና የእግር መንገድ ታሪክ ካርታ (StoryMap) ይጎብኙ።

ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ ወይም የአሜሪካ የአካል ጉዳተኛ ድንጋጌ (ADA)ን ጥያቄ ለማቅረብ የ SDOT ADA ፕሮግራም ድህረ-ገጻችንን ይጎብኙ።

የሁሉም ቪዲዮዎች ዝርዝር

ውስጥ በበረዶ እንዳይዘጋብን: እያንዳንዱ ሰው በደህና እንዲዘዋወር የእግረኛ መንገድዎን በረዶ በአካፋ ያንሱት

የግንባታ አካባቢ መዳረሻ: ለሁሉም ሰው አስፈላጊ ነው! 

ብስክሌት የሚጋሩበት ማቆሚያ: ትክክለኛውን ነገር ያድርጉ! 

መንገዱን አይዝጉ: የእግረኛ መንገድ ካፌ መመሪያዎችን መረዳት

ኮድ ወይም ደንብ ማግኘት

የሲያትል የእግረኛ መንገድ ንድፍ፣ ግንባታ እና የእንክብካቤ ስራዎች በሲያትል ማዘጋጃ ቤት ህጎች (SMC)፣ በዳይሬክተሩ ደንቦች እና በሌሎች የፖሊሲ ሰነዶች ይመራሉ። ከዚህ በታች ተዛማጅ ኮዶች እና ደንቦች ዝርዝር ናቸው።

የምስጢር ጽሑፎች/ኮዶች እና ደንቦች ዝርዝር

ለ20-አመት የሞዳል እቅዳችን ለመራመድ፣ ቢስክሌት ለመጋለብ፣ ለሕዝብ ማመላለሻ፣ እና ለጭነት፣ ለሪፖርቶች እና ጥናቶች እና የዳይሬክተር ደንቦች እና ድንጋጌዎች የሰነድ ቤተ -መጽሐፍታችንን ይጎብኙ።

ስለ የእግረኛ መንገድ ተግዳሮቶች ቪዲዮዎች

የእግረኛ መንገዶቻችንን ተደራሽነት ለመጠበቅ ከRooted in Rights ጋር ተከታታይ ቪዲዮዎችን ለማዘጋጀት/ለማምረት አብረን ሠርተናል። እርስዎ እንዴት መርዳት እንደሚችሉ አንዳንድ ጠቃሚ ጥቆማዎች እነሆ።

ውስጥ በበረዶ እንዳይዘጋብን: እያንዳንዱ ሰው በደህና እንዲዘዋወር የእግረኛ መንገድዎን በረዶ በአካፋ ያንሱት

የግንባታ አካባቢ መዳረሻ: ለሁሉም ሰው አስፈላጊ ነው! 

ብስክሌት የሚጋሩበት ማቆሚያ: ትክክለኛውን ነገር ያድርጉ! 

መንገዱን አይዝጉ: የእግረኛ መንገድ ካፌ መመሪያዎችን መረዳት

የእግረኛ መንገድ የንብረት ምንጮች እና የፕሮግራም ድህር አገናኞች

ከዚህ በታች በሲያትል የእግረኛ መንገድ መመሪያ ውስጥ የተካተቱት የሁሉም ፕሮግራሞች እና ግብአቶች ዝርዝር ነው።

ከዚህ በታች በሲያትል የእግረኛ መንገድ መመሪያ ውስጥ የተካተቱት የሁሉም ፕሮግራሞች እና ግብአቶች ዝርዝር ነው:

GIS ውሂብ እና መተግበሪያዎች

የታሪክ ካርታዎች

የድህር ጣቢያዎች

ሰነዶች 

ድጋፍ ይፈልጋሉ?

የሲያትል ከተማ አገልግሎቶችን ለማግኘት እና የእግረኛ መንገዶችን ተደራሽነት ለማሻሻል ብዙ የሚረዱ ፕሮግራሞች አሏት።

SDOT ADA ፕሮግራማችን በሲያትል ውስጥ እየኖሩ ያሉትን የአካል ጉዳተኞችን እኩል የእግረኛ ንብረቶችን እንዲያገኙ ለማስቻል በህዝብ የተጠየቁ ማሻሻያዎችን የማቀድ፣ የመንደፍ እና የመተግበር ሃላፊነት አለበት። እነዚህ ማሻሻያዎች የኩርባ መወጣጫዎችን፣ የእግረኛ ተደራሽነት ምልክቶች (APS)ን፣ እና አዲስ የቴክኖሎጂ ግምገማዎችን ያካትታሉ። የበለጠ መረጃ ወይም የ ADA ጥያቄ ለማቅረብ ከፈለጉ የ SDOT ADA ፕሮግራም ድህረ ገጽን ይጎብኙ።

በ2016፣ ሲያትል የዓለም ጤና ድርጅትን እና AARPን ለዕድሜ ተስማሚ የሆኑ ከተሞች እና ማህበረሰቦች በዓለም-አቀፍ ተብሎ የተሰየመ አውታረ መረብ ተቀላቀለ። በዕድሜ ተስማሚ የሚባሉ ከተሞች ከቤት ውጭ ባላቸው ቦታዎች እና ሕንፃዎች፤ በመጓጓዣ፤ በመኖሪያ ቤት፣ በማህበራዊ ተሳትፎ፤ በመከባበር እና በማህበራዊ ማካተት፤ በሲቪክ ተሳትፎ እና ሥራ፤ በመገናኛ እና መረጃ እና በማህበረሰብ ድጋፍ እና የጤና አገልግሎቶች ተለይተው ይታወቃሉ።  ስለ ፕሮግራሞቹ የበለጠ ማወቅ ይፈልጋሉ? Age Friendly Seattleን ይጎብኙ ወይም በኢሜል agefriendly@seattle.gov ያግኙን።

ስለማህበረሰብ የሀብት ምንጮች እና የአገልግሎት አማራጮች ነፃ፣ ተጨባጭ ዓላማ ያለው፣ ሚስጥራዊ መረጃን ለማግኘትየማህበረሰብ አኗኗር ግንኙነቶችን ያግኙ ወይም በ 1 (844) 348-5464 ይደውሉ።

የቤት ጥገና ፕሮግራም

የቤት ጥገና መርሃ ግብሩ ገቢያቸው ብቁ ላደረጋቸው የቤት ባለቤቶች ወሳኝ የሆነ የጤና፣ የደህንነት እና የመዋቅራዊ ጉዳዮችን ለመፍታት በዋጋ ተመጣጣኝ ብድሮችን ይሰጣል።

የፍጆታ መገልገያዎች ቅናሽ ፕሮግራም

የፍጆታ መገልገያዎች ቅናሽ ፕሮግራም ለአረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች እና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ደንበኞች የክፍያ ድጋፍን ይሰጣል።

RainWise

የኪንግ ካውንቲ የቆሻሻ ውሃ አያያዝ መምሪያ እና የሲያትል የህዝብ መገልገያዎች አረንጓዴ የዝናብ ውሃ መሠረተ መዋቅርን (GSI) ወደ ሰፈሮቻችን ለማምጣት እና በተፈጥሮ የዝናብ ውሃ ከላይ መግረፍን ለማስተዳደር በጋራ እየሰሩ ነው። የበለጠ ለማወቅ የ RainWise ፕሮግራምን ይጎብኙ።

ነፃ የመጸዳጃ መቀመጫ አገናኝ

የሲያትል የህዝብ መገልገያዎች ገቢያቸው ብቁ ለሚያደርጋቸው የቤት ባለቤቶች ነፃ የውሃ ቆጣቢ መጸዳጃ ቤቶችን ይሰጣል።  

ማስተባበያ

©2022፣ በሲያትል ከተማው፣ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። በሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT) የተዘጋጀ/ የተራባ። የሲያትል ከተማ ለትክክለኛነቱ ምንም አይነት ውክልና ወይም ዋስትና፣ በተለይም ስለትክክለኝነቱ አሰያየም፣ ልኬቶች፣ ቅርጸቶች፣ የንብረት ድንበሮች፣ ወይም የትኛውንም ከዚያ ውስጥ የተገኘ የካርታ ባህሪ አቀማመጥ ወይም አካባቢ/ አድራሻ አይሰጥም። የትክክለኛነት፣ የብቃት ወይም የመገበያየትን ጨምሮ፣ ከዚህ ምርት ጋር ምንም አይነት ዋስትናዎች የሉም። የውሂብ ስብስቦች አጠቃላይ፣ የተገደበ መረጃ ይይዛሉ እና የንብረት ወሰኖችን ወይም የላይ ላዩን ገፅታዎችን ለማግኘት ወይም ለመወሰን ጥቅም ላይ መዋል አይችሉም። 

Transportation

Greg Spotts, Director
Address: 700 5th Ave, Suite 3800, Seattle, WA, 98104
Mailing Address: PO Box 34996, Seattle, WA, 98124-4996
Phone: (206) 684-7623
684-Road@seattle.gov

Newsletter Updates

Subscribe

Sign up for the latest updates from Transportation

The Seattle Department of Transportation (SDOT) is on a mission to deliver a transportation system that provides safe and affordable access to places and opportunities for everyone as we work to achieve our vision of Seattle as a thriving, equitable community powered by dependable transportation.